Yehadola Lijochይህ የወደፊቱ የአዶላና ክብረመንግስት ዌብሳይት ሲሆን በተለይ የሚያተኩረው በአካባቢዋ ስለሚገኙት ልጆች ሁናቴ ይሆናል። በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እነዚህን ልጆች በተቻላቸው መጠን በመርዳት ላይ ይገኛሉ።

አደቆርሳ እንደጻፈው

የግል ሪፖርትሽን አንብቤ ምን እንደምልና ከምን እንደምጀምር ግራ ገባኝ ::
እነዚህ የእግዚአብሄር ፍጡሮች ልቦና ውስጥ ለሴኮንዶች ያህል በቆየሁና ስሜታቸውን ባደመጥኩ !ብዬ አሰብኩ :: በእውነት በጣም ደስ አለኝ :: ኮራሁባችሁ እናንተ ልጆች አንተ ደጉ የሚሉህ አልፎ አልፎ ቦሬ የምናይህ ነህ ? ያቺ የሲዳማ ሴት ጡቶቿን በሁለት እጆቿ ይዛ የመረቀችህ ነህ ? እኔ ባውቅህ ምን እጨምርልሀለሁ የሚያውቅህ አምላክ እርሱ ይጨምርልህ ! ያዘጋጀኸውን መጽሄት ራስብሩ ልኮልኛል ግን እስካሁን አልደረሰኝም ::

ሰሞኑን ቅሩንፉድዬ ፖስት ካደረገችው ጥቅስ ውስጥ አንዱ እንዲህ ይላል

"ችግርና መከራ የሌለበት ህይወት አትመኝ በዛ ምንም አይገኝምና ::"

እውነት ነው እግዚአብሄርም በሀዋርያት ሥራ ላይ በብዙ ድካምና መከራ ወደእግዚአብሄር መንግሥት እንድንገባ አሳስቦናል ቁጭ ብሎ ነግሻለሁ ማለት ስንፍና ነው :: እናንተ በድካማችሁ የምታደርጉት ሁሉ ፍሬው ትርፍ አለውና ሁሌም ደስ ይበላችሁ :: ይህ ቀላል ነገር አይደለም ሁላችሁም ቤተሰብ አላችሁ ሁላችሁም የተቸገረ ዘመድ ይኖራችኍል እርግጠኛ ነኝ እዛም ሁሌ አግኝታችሁ ሀሳባችሁ ሞልቶ አያውቅ ይሆናል ይህም ሁሉ ሆኖ ግን ከምታገኟት ላይ ለነዚህ ተስፋ ላጡ ወላጆቻቸውን ለማያገኙ ሰጪና ደጋፊ ለሌላቸው ህጻናት የምታደርጉት ከሁሉ በላይ ዋጋ አለው :: ተባረኩ እናንተ ሰዎች :: በሌላም በኩል እነዚህ ህጻናት ውስጣቸው ተስፋ እንዲሞላ ትምህርታቸውን ጠንክረው እንዲማሩ ለኮሚቴዎቹ በደንብ ማሳወቅ ይኖርብናል :: በተለይ እናንተ ከዛ ስትደውሉ የተሻለም ስለሚሆን የአቶ ደበበ ወይንም የሌሎቹን አድራሻ ከዚህ በፊት ራስብሩ ለጥፎት ነበር በመደወል አንዳንድ ሀሳቦችን መለዋወጡ መልካም ነው ብዬ አምናለሁ ::

ክብር ለእግዚአብሄር ይሁን !!!

መሬት ቁጢጥ ብሎ በሁለት እጆቹ አገጩን ይዞ የሚታየውን ልጅ እስቲ ተመልከቱት አንጀት አይበላም ? ዳሩ ማን አንጀት የማይበላ አለ ::