Ato Yimam

በክብረ መንግሥት ልጆች ታሪክ ታላቅ ስፍራ ያለውን :የብዙ ወጣቶች ደም በከንቱ እንዳይፈስ ተጋድሎ ያደረገውን : ከነዚያ ከህዝብ ድርጅቶች ወጥመድ እንዲያመልጥ ወጣቱን የታደገውን ምስኪን አብዮት ጠባቂ ጋሽ ይማምን ከምነም በላይ አወደሰችው ::ይህ ሰው በህይወት አለ ?
አይ ያንቺ ነገር ለነገሩ በህይወት የለም ::እኔንያቆየላት ይማሙ የመሰላት ያህል ትንሽ አ ......ች ::
በታህሳስ 4ቱ የመጀመሪያው የኢሀፓ እስረኞች ከነበሩት አንዱ ነበርኩ :: በፖሊስ ጣቢያ ሳለን አንድ ቀን እንዲህ ሆነ :ከምሽቱ 4ሰዓት ይሆናል በራችን ተበረገደና አንዱ እስረኛ ወደውስጥ ተገፍትሮ : ተጠረቀመ ::ማን እንደሆን እና እንዴት እንደታሰረ ሁሌ ማታ ማታ ውጭ የሚሆነውን ለመስማት እንዲያመች ሰለምናዳጥ አውቀን ነበርና ተነጋግረን እየጠበቅን ሳለን ነበር ወደኛ ክፍል የጨመሩት ::

እንግዲህ ያውላችሁ እንደሚሆን አርጉት ነው ነገሩ ::
ወዲያው አፉን እፍን አድርገን እንዳይሞት እንዳይሽር ካደረግነው በኍላ ራሳችን መጮህ ጀመርን :: ነፍሱን ይማረውና ሚካኤሌ የሚባል ፖሊስ ነበርና ወዲያው ለዋናው አዛዥ ለሻምበል ኢዮብ ደወለና መጡ :: ሁላችንንም ራቁታችንን ወደውጭ እንድንወጣ እና ዝናብም ስለነበረ በደረታችን እንድንተኛ ታዘዘ ራቁታችንንም ዝናብ ላይ ተኛን ::
ከሴቶቹ ክፍልም ጩኸት ተስተጋባ ወንድሞቻችን ላይ:: ምንም ዓይነት ነገር እንዳይፈጸምባቸው !!!! ሁኔታውን ግን ያውቁ ነበር :: ትንሽ እንደተቀጣን ከመሀላችን አንዱ የሆነውን እንዲናገር ሲፈቅዱ ሱሌማን መሀመድ ተነሳና መናገር ጀመረ :: ሁለተኛው ተናጋሪ ሲሳይ ሳንታ ነበር :: ይሄው እሱ በስልጣኑ ተመክቶ ወላጆቻችን ደክመው ያመጡልንን ስንቅ ደፋፍቶ ሁላችንንም እየደበደበ አላስተኛ ስላለን ጮህን በማለት ሲናገር አውጣው ብለው ወታደሩን አዘዙ : ወታደሩ ሲያወጣው እሱ ምንም አያውቅም ነበር :: እኛም ተራ በተራ ቧንቧው ጋ እየታጠብን ወደየክፍላችን ገባን :: በማግሥቱ ንጉሴ እና መልካሙ ፖሊስ ጣቢያው በረንዳ ላይ ቆመው ሳለ ጋሽ ይማም ተጠርቶ መጣ:: ንጉሴ ቀረብ አለና ያንን በክሳት የሰረጎደ ጉንጩን በጥፊ ሊለው ሲንደረደር ሻምበል ኢዮብ አስቆሙት :: ትናንት ማታ ያንን የህዝብ ድርጅት አባል ሰክሮ ሲወላገድ አግኝቶ በሰዓት እላፊ አስሮ ወደጣቢያ ያመጣው ጋሽ ይማም ነበር :: ብቻውን መታሰር የለበትም ብሎ እኛ መሀል ሲከተውም ይህ እንደሚሆን ያውቅ ነበር ::
ከአራዳ ለመንክር ብርሀኔ እና ለአየለ አራርሳ የህይወት ባለውለታ ነው ::እኔንም በጠፍ ጨረቃ ከወዩ እንድወጣ ያስደረገኝ ጋሽ ይማም ነበር :: ብዙ ያደረጋቸውን ነገሮች ባወጋችሁ ደስ ባለኝ ግን አይቻለኝም ::
ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ሳጫውታት አንዳንዴ ግራ ይገባትም ነበር :: በመጨረሻ ግን ምን አለቺኝ መሰላችሁ (ቆይ ግን እድሜህ ስንት ነው ?)

በሉ ቸር ይግጠመን ወገኖቼ ::

ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ ነኝ ::